የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ነገሮች

ከአማካሪው ጋር • 15 ትምሕርቶቹን • 7 ተማሪዎቹን

መግቢያ፡-  መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምሕርት

ይህ ኮርስ 15 ትምሕርቶችን የያዘ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና ዋና አሳቦች፣ ማለትም እግዚአብሔር ላንተ ያለውን መልእክት ያሳይሃል፡፡ በእያንዳንዱ ትምሕርት መጨረሻ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ለምላሾችህ አስተያየቶችን የሚለግስህ እንዲሁም ተጨማሪ ጥያቄዎችን ልታነሳለት የምትችለው የግል አማካሪ ይኖርሀል፡፡

አማካሪህ አብዛኛውን ጊዜ ለጥያቆዎችህ ከ24-48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ ይሰጥሀል፡፡ በኮርሱ ማጠናቀቂያ አማካሪህን የሚያረካ ሥራ መሥራት ከቻልህ ሠረተፊኬት ታገኛለህ፡፡ በቀን ውስጥ 1 ወይም 2 ትምሕርቶችን እንድታጠና እንመክርሀለን፡፡ ይህ የትምህርቶቹን መንፈሳዊ ጭብጥ በጥልቀት እንድታሰላስል እንዲሁም ከግል አማካሪህ ጋር ስለ ጥያቄዎችህና መንፈሳዊ ሕይወትህ እንድትነጋገርና ከርሱም ጋር ያለህን ግንኙነት እንድታጎለብት ያስችልሀል፡፡

አጠቃላይ ኮርሱን ለማጠናቀቅ በርከት ያሉ ሳምንታትን ብትጠቀም ራስህን የተሻለ ትጠቅማለህ፡፡

ትምህርቱን እንደምትወደውና ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ ለመጠጋት እንደሚያስችልህ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

የተማሪው አስተያየት ስለዚህ ኮርስ

‹‹በዚህ ኮርስ ለኔ እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ያገኘሁት፣ አማካሪዬ አንድን አሳብ በበለጠ መረዳት እንድችል እኔን ማገዙና እና ጥያቄዎቼን መመለሱ ነው፡፡ ስለዚያም፣ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡››

እባክዎ ከ1 ወይም 2 ትምሕርቶች በላይ በአንድ ጊዜ ሰርተው ለእርማት አይላኩ፡፡ አማካሪህ ስለ ትምሕርትህ አስተያየቶችን እንዲለግስህ እድል ስጠው፤ የአማካሪህ ምላሽ አብዛኛውን ጊዜ በ 48 ሰዓታት ውስጥ ይደርስሀል፡፡

ይህን ትዕዛዝ ካላከበሩ የሰሩት አይታይልዎትም!

እናመሰግናለን!

ኮርሱን ይጀምሩ